ንብረት በሚከራዩበት ጊዜ መብቶችና ሃላፊነቶች አለዎት። በዚህ ገጽ ላይ ቤት በሚከራዩበት ጊዜ መመሪያዎችን መስጠትና ካስፈለግዎት የበለጠ መረጃ እንዲያገኙ ይረዳል።
በ 2021 ዓ.ም ጠቃሚ በሆኑ የቤት ክራይ ህጎች ላይ ለውጦች በቪክቶሪያ ተካሂዷል። ስለ አዲስ ደንቦች/the new rules ማንበብ።
በዚህ ገጽ ላይ:
ንብረቱ ለርስዎ ትክክለኛ ስለመሆኑ መወሰን
በሆነ ሰው ንብረት ላይ ተከራይቶ ለመኖር በሚገቡበት ጊዜ ለመኖሪያ ክራይ ስምምነት ውል ገብተዋል። ይህ ህጋዊ የሆነ ስምምነት ውል ሰነድ እንደሆነ እና ውሉ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜ ሊካሄድ ስለሚችል ስለዚህ ንብረቱ በቀጥታ የርስዎ እንደሆነ እምነትም ያሳድርልዎታል።
በኪራይ ውል ስምምነት ላይ ከመግባትዎ በፊት በኪራይ አቅራቢ (ባለንብረቱ) በኩል አንዳንድ መረጃዎች ለርስዎ ማቅረብ አለበት። እነዚህ ግዴታዊ መግለጫዎች ይባላል። ከዚህ በታች ያሉት በዚህ ይካተታል:
- የኪራይ አቅራቢው ንብረቱን ለመሸጥ ከንብረት ተወካይ ጋር ግንኙነት ካለው ወይም ንብረቱ በኮንትራት ለመሸጥ ዝግጅት ላይ ከነበረ ነው።
- የንብረቱ ባለቤት ከሆኑ ወይም ካልሆኑ በንብረት ማከራየት ላይ መብት ካላቸው።
- በሚከራየው ንብረት ወይም በጋራ መጠቀሚያ ንብረት ላይ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ በአካባቢው የነብስ ማጥፋት ድርጊት ከነበረ። .
- በሚከራየው ንብረት ላይ ማንኛውም አስበስቶስ ካለበት።
ስለ አስፈላጊ የሆነ ግዴታዊ መግለጫ መስጫ ለበለጠ መረጃ በድረገጽ ለስምምነት በሚፈርሙበት ጊዜ ለማወቅ ያለዎት መብቶች/ Knowing your rights when signing an agreement ውስጥ ገብቶ ማየት።
በኪራይ አቅራቢዎች በኩል አድልዎ ፈጠራ
ቪክቶሪያ ውስጥ በአንዳንድ ግላዊነት ባለው ለይቶ ጥላቻ ባህሪ ተመርኩዞ አድልዎ መፍጠር ህገወጥነት ይሆናል። ይህ ማለት የኪራይ አቅራቢዎች እና የንብረት ተወካዮች ለርስዎ መጠለያ ቤት መስጠት እምቢ ማለት አይችሉም ወይም በርስዎ አከራይና ተከራይ ውል መሰረት ለተቀመጠ የግላዊነት ጥላቻ ባህሪ ማሳየት ህግን በመጣስ በርስዎ ላይ አድልዎ ፈጠራ ይሆናል።
ለንብረት ኪራይ በሚያመለክቱበት ጊዜ፤ በሚገቡበት ወይም ንብረቱን በሚለቁበት ጊዜ በኪራይ አቅራቢ ወይም በንብረት ተወካያቸው እርስዎን አላግባብ ማስተናገድ ወይም ባለዎት ግላዊ ባህሪ ጥላቻ ተመርኩዞ አድልዎ መፍጠር ህገወጥነት ነው።
ለቤት ኪራይ በሚያመለክቱበት ጊዜ እንደ የማመልከቻ ቅጽ አንዱ ክፍል፤ ስለ አድልዎ ፈጠራ ስለ ንብረት ኪራይ መረጃ በንብረት ተወካዮች በኩል መሰጠት ይኖርበታል።
በሚከራዩበት ጊዜ ስለ አድልወ ፈጠራ የበለጠ መረጃ በሚከራዩበት ጊዜ ህገወጥ አድልወ ፈጠራ/Unlawful discrimination in renting ላይ ማየት።
የኪራይ አቅራቢው መጠየቅ የማይችለው ጥያቂዎች
ለንብረት ኪራይ የሚያመለክቱ ከሆነ የኪራይ አቅራቢው እርስዎን መጠየቅ የማይችለው:
- ቀደም ሲል ከኪራይ አቅራቢ ጋር (ወይም ሌላ የመኖሪያ ቤት አቅራቢ) ክርክር ከነበረብዎት
- ከርስዎ የማስያዣ ገንዘብ ጋር በተዛመደ ጥያቄ አድርገው ከነበር
- በክረዲት ወይም ባንክ ጽሁፍ መግለጫ ላይ የተካተተ በየቀኑ ለወጣና ለገባ ገንዘብ - ኪራይ አቅራቢው ለጽሁፋዊ መግለጫ መጠየቅ ይችላል ነገር ግን የርስዎን ግላዊነት ለመከላከል በጽሁፋዊ መግለጫ ያሉትን አንዳንድ የወጣና የገባ ማስወገድ አይችሉም።
- the በእኩልነት እድል አንቀጽ ህግ/Equal Opportunity Act 2010 ዓ.ም መሰረት መረጃ አውጥቶ ለመስጠት ምክንያት በጽሁፍ ካልቀረበ በስተቀር ስለ የተጠበቀን መለያ ባህሪ ማንኛውንም መስጠት አይቻልም።
አንዳንድ የኪራይ አቅራቢዎች ከሌላ ምንጮች መረጃዉን ያገኛሉ። ነገር ግን ለቤት ንብረት ስለማመልከትዎ መረጃ ከርስዎ ለማግኘት መጠየቅ አይችሉም።
የኪራይ ውል ስምምነት ስለመጀመር
ከአንድ ሰው ተከራይተው ለመኖር ውል ስምምነት በሚያደርጉበት ጊዜ በመኖሪያ ኪራይ ቤት ስምምነት ውስጥ ገብተዋል (አንዳንዴ እንደ ውል ኩንትራት ወይም የተከራይና የአከራይ ስምምነት ይባላል)።
ስምምነቱ በጽሁፍ ወይም በቃል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ስምምነቱ በጽሁፍ ቢደረግ የበለጠ የተሻለ ነው።
የኪራይ ስምምነት በርስዎና በኪራይ አቅራቢ መካከል የሚካሄድ ኮንትራት ነው። በነዚህ የሚገለጽ:
ለኪራይ ስምምነት በጽሁፍ አድርጎ ሲወሰድ ‘ለመግለጫ ያለውን ቅጽ’ መጠቀም አለብዎት። መግለጫ ቅጹ የሚገለጸው በቪክቶሪያ የኪራይ ህግ መሰረት ነው። የእኛን ህጋዊ ቅጽ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
በአምስት ዓመት ወይም ከዚያ በታች ለተወሰኑ ስምምነቶች፤ የእኛን ህጋዊ ቅጽ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
ቅጽ 1።
ከአምስት ዓመት በላይ ለሚቆይ የተወሰኑ ስምምነቶች፤ የእኛን ህጋዊ ቅጽ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
ቅጽ 2።
አከራዩ ወይም የኪራይ አቅራቢ በመኖሪያ ተከራይና አከራዮች አንቀጽ ህግ/ Residential Tenancies Act ያለውን እስከተከተሉ ድረስ በኪራይ ስምምነት ውሉ ውስጥ ተጨማሪ ሁኔታዎችን ወይም ደንቦችን ማስገባት ይችላሉ።
ለምሳሌ፡ የኪራይ አቅራቢው በንብረቱ ውስጥ ስለ ሲጋራ አለማጨስ ደንብን ማካተት ይችላል። ወይም አከራዩ መጠየቅ የሚችለው የጋዝ መሳሪያዎች በሙሉ በየሁለት ዓመቱ እድሳት መደረግ እንዳለበት ለሚል ደንብ ማካተት ይችላል።
በስምምነት መስጫ ላይ መፈረም ያለብዎት በኪራይ ስምምነት ውል ላሉት ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም እንደ ተከራይ መሆንዎ ላለዎት መብቶችና ሃላፊነቶች ከተረዳዎትና ከተስማሙ ብቻ ነው።.
ያልተረዳዎት የሆነ ነገር ካለ ማብራሪያ እንዲደረግልዎት ለእኛ ማነጋገር/contact us ይችላሉ።
ወደ ንብረቱ ከመግባትዎ በፊት
ወደ ንብረቱ ከመግባትዎ በፊት የርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ ለርስዎ ማቅረብ ያለበት:
- ለርስዎ የኪራይ ስምምነት ውል ቅጂ
- በስምምነቱ ላይ ለፈረመ ለእያንዳንዱ ተከራይ ቁልፎችን ማቀናጀት
- ለንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት (መክፈል ካስፈግዎት የማስያዣ ገንዘብ)
- ምናልባት አስቸኳይ የቤት ጥገና ካስፈለግዎት ለርስዎ ዝርዝር አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ይሆናል።
ወደ ንብረቱ በሚገቡበት ጊዜ ለውሃ፤ ኤሌትሪክ፤ ጋዝ እና ተለፎን አገልግሎቶችን ለመጠቀም የማስቀጠል እቅድ ለማቀናጀት እነዚህን ኩባንያዎች ማነጋገር አለብዎት። እነዚህን አገልግሎቶች ለማቀናጀትና በርስዎ ስምምነት ሌላ ካልሆነ በስተቀር ክፍያዎችን ማካሄድ የርስዎ ሃላፊነት ነው።
ለበለጠ መረጃ ለመገልገያና አገልግሎቶች ማቀናጀት/Setting up utilities and services የሚለውን ማየት።
እንዲሁም በበለጠ መረጃ ለማግኘት በእኛ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ስምምነት ቅጽ/ residential rental agreement form. ላይ ማግኘት ይችላሉ።
በሚከራይ ንብረት ላይ አነስተኛ ደረጃዎች
በሚከራይ አነሰተኛ ደረጃዎች መሰረት በንብረቱ ጥገና እንደተደረገ እርግጠኛ መሆን የርስዎ ኪራይ አቅራቢ ማረጋገጥ አለበት። እርግጠኛ ስለመሆን በዚህ የሚካተት:
- በንብረቱ ላይ ዝገት፤ ተባይ ወይም ትላትል መኖር የለበትም
- አሁን ያለው መሳሪያ እንደ ምድጃ ኦቨንና ስቶቭ በሚገባ መስራት አለባቸው
- ደህንነቱ የተጠበቀ የሚሰራ ማሞቂያ መኖር
- ለኩሽና ቤትና ለሰውነት መታጠቢያ ክፍል የሚሆን ብቃት ያለው የሙቅ ውሃ አቅርቦት መኖር
- የንብረቱ ቅርጽ አወጣጥ ለደህንነትና ለአየር ማረጋገጫ ደህንነት ያለው ነው።
የሚከራየው ንብረት አነስተኛ የሆኑትን ደረጃዎች ካላሟላ ወደ ንብረቱ ከመግባትዎ በፊት የኪራይ ስምምነቱን ውል ማፍረስ ይችላሉ። እንዲሁም ወደ ንብረቱ ከገቡ በኋላ በማንኛውም ጊዜ አነስተኛ ለሆኑት ደረጃዎች እንዲሟላ አስቸኳይ ጥገና እንዲደረግ መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ: ይህ ተግባራዊ የሚሆነው ከቀን 29 መጋቢት/March 2021 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለኪራይ ስምምነት ውል መፈረም ይሆናል። የርስዎ ኪራይ ስምምነት ውል ከዚህ ቀን በፊት ተፈርሞ ከሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በእኛ ወደ አዲስ የኪራይ መሸጋገር ህጎች ገጽ/Transition to new renting laws. ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ስለ አነስተኛ ደረጃዎች የበለጠ መረጃ በኪራይ ንብረቶች አነስተኛ ደረጃዎች/Minimum standards for rental properties ላይ ማየት።
የማስያዣ ገንዘብ ስለመክፈል
አብዛኞቹ ኪራይ አቅራቢዎች ወደ ንብረቱ ከመግባትዎ በፊት የማስያዣ ክፍያ/ pay a bond ይጠይቃሉ፤ ስለዚህ በንብረቱ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ጕዳት ካደረሱ ለዚህ መሸፈኛ ገንዘብ አለ።
በንብረቱ ላይ ምንም ዓይነት ጕዳት ካላደረሱ፤ ከቤት በሚወጡበት ጊዜ የማስያዣ ገንዘቡ ይመለስልዎታል።
በንብረቱ ላይ ጕዳት ካደረሱ፤ ከቤት በሚወጡበት ጊዜ የተበላሸውን ለማስጠገን ክፍያ እንዲሆን የማስያዣ ገንዘቡን ወይም በከፊሉ የኪራይ አቅራቢው ሊጠቀምበት ይችላል።
የማስያዣ ገንዘቡ የሚቀመጠው የርስዎ ስምምነት ውል እስኪያልቅ ድረስ በ Residential Tenancies Authority (RTBA), ላይ እንደሆነ፤ ይህም በማንም ተጽእኖ የሌለበት በራሱ የሚመራ ድርጅት ነው። የኪራይ አቅራቢው ከቤቱ ከለቀቁ በኋላ ገንዘቡን ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር ከዚያ በፊት ገንዘቡን መጠቀም አይችልም።
የርስዎ ኪራይ አቅራቢ የማስያዣ ገንዘብን ከወሰደ፤ ማድረግ ያለባቸው:
- ገንዘቡን ወደ RTBA ማስገባት
- ለማስያዣ ገንዘብ ማስገቢያ ቅጽ እንዲፈርሙበት መስጠት
- የንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት ማዘጋጀት ይህም ንብረቱ ያለበትን አጠቃላይ ይዘት ሁኔታን ይመዘግባል
የርስዎ ማስያዣ ገንዘብ እንደገባ የሚያሳይ ከ RTBA ደረሰኝ ያገኛሉ። የርስዎን ማስያዣ ገንዘብ ደረሰኝ ደህንነት ባለው ቦታ ስለመቀመጡ ያረጋግጡ። የርስዎ ማስያዣ ገንዘብ ከከፈሉ በ15 ቀናት ውስጥ ደረሰኝ ካልተላከልዎት ለ RTBA ማነጋገር።
የይዘት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት
የይዘት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት/condition report ማለት በቤቱ ላይ በሚገቡበት ጊዜ የንብረት ሁኔታ ይዘት መለጫ ምዝገባ ይሆናል።
በንብረቱ ላይ በወቅቱ ማንኛውም ችግሮች ማለት እንደ የሆነ የተሰበረ ወይም የተበላሸ ካለ መገልጽ አለበት።
ከቤት በሚወጡበት ጊዜ በንብረቱ ላይ ጉዳት አድርሰው ከሆነ (ምክንያታዊ የሆነ ማርጀትና መበርበርት ተብሎ በሚጠራ፤ ከመደበኛ ፍጻሜ ጥራት ማነስ ማለት በእያንዳንዱ ቀን ላይ በመጠቀም ለሚፈጠር የአነስተኛ ጥራት ማነስ ካልሆነ በስተቀር) ከሁኔታ ይዘት መግለጫ ሪፖርቱ ጋር ለማመዛዘን ይጠቅማል።
በንብረቱ ላይ ከመግባትዎ በፊት የሁኔታ መግለጫ ሪፖርት ለተፈረመበት 2 ቅጂዎች (ወይም በኤሊትሮኒክስ ቅጂ) በእርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ በኩል ለርስዎ መስጠት አለበት። የሁኔታ መግለጫ ሪፖርት በሚሰጥዎ ጊዜ ማድረግ ያለብዎት:
- የንብረቱን ደህንነት መፈተሽ እና ስለማንኛውም የደህንነት ችግሮች (እንደ የተሰበረ የገንዳ አጥር ወይም ኤሌትሪክ ችግሮች) ካሉ ለኪራይ አቅራቢ ወይም ለንብረት ተወካዩ መናገር።
- ሁለቱን ቅጂዎች ሪፖርት መሙላት። ማሳሰቢያ፤ በወቅቱ የሆነ ጉዳት እንደ በግድግዳ ላይ የተሰነጠቀ፤ ምልክት ወይም የእጀታዎች መሰበር ካለ መመዝገብ። እንዲሁም በሪፖርቱ ውስጥ የኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ በጻፈው ላይ ካልተስማሙበት ማስታወሻ ማስቀመጥ ይችላሉ።
- ለእቃዎች፤ ግድግዳ ላይ ለተለጠፉና የተገጠሙ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶ ማንሳት።
- ወደ ቤት ከገቡ በ 3 ቀናት ውስጥ የተፈረመበትን የሁኔታ ይዘት መግለጫ ሪፖርት አንደኛውን ለርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ መልሶ መስጠት።
- ሌላውን ቅጂ መያዝና ደህንነት ባለው ቦታ ላይ ማስቀመጥ። ከቤት በሚለቁበት ጊዜ ሊያስፈልግዎት ስለሚችል ታዲያ የርስዎን ማስያዣ ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ።
በተከይነት ስምምነት ጊዜ
በተከራይነት ስምምነት ጊዜ በተከራየው ንብረት ላይ አንዳንድ መብቶችና ሃላፊነቶች አለዎት።
- በጊዜው የርስዎን ቤት ኪራይ መክፈል። ለእያንዳንዱ የቤት ኪራይ ክፍያ ደረሰኝ ማግኘት ይችላሉ።
- ንብረቱን በተገቢው ንጽህናን መጠበቅ። ንጽህናውን ካልጠበቁ፤ ወይም በንብረቱ ላይ ጉዳት ካደረሱ ታዲያ ከቤት በሚለቁበት ጊዜ ሙሉ የማስያዣ ገንዘብ ላይመለስልዎት ይችላል።
- ለርስዎ የጎረቤታሞችን ሰላምና ግላዊነት ማክበር፤ እንዲሁም የርስዎ እንግዶችም እንደዚያው።
- ስለሚፈልጉት ማንኛውም ጥገና ለኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ መናገር።
- በንብረቱ ላይ ትንሽ ለውጦች ማድረግ ሲችሉ እንደ የስእሎች ፍሬም መያሻ ሜንጦዎችን ማስቀመጥ ይችላሉ። ነገር ግን ከኪራይ አቅራቢው ስምምነት ካላገኙ እንደገና እድሳት ንብረቱን መቀየር ወይም እንደገና ማስጌጥ/alter or redecorate the property ማካሄድ አይችሉም።
የርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ ወደ ንብረቱ ለመግባት መብት አላቸው፤ ነገር ግን ለምን መግባት እንደፈለጉ በጽሁፍ አድርገው ቢያንስ የ24 ሰዓት ማሳሰቢያ መስጠት አለባቸው።
የኪራይ አቅራቢ ወይም ንብረት ተወካዩ ወደ ንብረቱ መግባት የሚችሉበት ጠቃሚ ምክንያቶች ዝርዝር/list of valid reasons a rental provider or agent can enter the property እንዳለ ነው። እንዲሁም ወደ ንብረቱ መግባት የሚችሉት ስምምነት በተደረገበት ቀንና ሰዓት ይሆናል። የንብረት ማጣራት ፍተሻ የሚያካሂድ በኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ ብቻ ሲሆን ይህም የማጣሪያ ፍተሻ የሚካሄደው በየ 6 ወራት አንዴ፤ እና ከቤቱ ከገቡና መኖር በመጀመሪያ 3 ወራት የመጀመሪያ ፍተሻ ማጣሪያ ማካሄድ አይቻልም።
በመለወጥ ማስተካከል
መጀመሪያ የኪራይ አቅራቢ ወይም ንብረት ተወካዩ ስምምነት ሳያደርግ፤ በተከራዩበት ንብረት ላይ አንዳንድ የለውጥ ማስተካከል ለማድረግ መብት አለዎት። በዚህ የሚካተት:
- በግድግዳ ላይ የስእል መያሻ ሜንጦ ወይም በምስማር ማያያዣ ማስገባት፤ በተጋለጠ ጡብ ወይም የስሜንቶ ግድግዳ ሳይሆን በሌላ ገጽታዎች ላይ መደርደሪያዎች ወይም መጽሀፍ ማስቀመጫ ማስገባት።
- በውሃ ላይ ብቃት ላለው የሰውነት መታጠቢያ ጭንቅላትን በማስገባት የመጀመሪያው የመታጠቢያው ጭንቅላት እንዳለ ይቆያል።
- መጋረጃ ብላይንድ ወይም መቀባበያ ኮርድ አንቾር ማስገባት።
ሌሎችም እንዳሉ እና እነዚህ በበለጠ ለሚቆይ መስተካከያ ለውጦች ከኪራይ አቅራቢ ወይም ንብረት ተወካዩ ስምምነት እንደሚፈልግ፤ ይሁን እንጂ የነሱን ስምምነት ለመስጠት እምቢ ለማለት ምክንያታዊ መሆን አለባቸው። የነዚህ ማስተካከያ ለውጦች ዝርዝራቸው እዚህ/here ማግኘት ይቻላል።
የማስተካከያ ለውጥ ካደረጉ፤ እና ከርስዎ ኪራይ አቅራቢ ጋር ስምምነት ስምምነት ከሌለ በስተቀር የቤት ኪራይ ስምምነት ጊዜ ከመድረሱ በፊት ንብረቱ ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ ይኖርብዎታል።
ስለ ማስተካከያ ለውጥ ማድረግ፤ ስለ ኪራይ አቅራቢ ስምምነት ላለመስጠት ያለው መብትን በተመለከተ የበለጠ መረጃ በንብረቱ ላይ ተከራዮች ለውጦች ማድረግ/ Renters making changes to a property ላይ ማየት።
ጥገና ስለማካሄድ
በንብረቱ ላይ የተሰበረ ወይም የተበላሹ ነገሮች ካሉ ጥገና እንዲደርግልዎት የማድረግ መብት አለዎ። ጕዳቱን እርስዎ ካላደረሱ (ለምሳሌ፡ የርስዎ ማሞቂያ ከተበላሸ) መክፈል የለብዎትም። ጕዳቱን እርስዎ ካደረሱት የማስጠገኛ ገንዘቡን እርስዎ መክፈል ይችሉ ይሆናል።
ለርስዎ ጥገና እንዲደረግ ስለጠየቁ፤ ያለዎትን ኪራይ ስምምነት ውል የርስዎ ኪራይ አቅራቢ እንዲቆም ማድረግ አይችልም።
ጥገናዎች አስቸኳይ ወይም አስቸኳይ ላይሆኑ ይችላሉ። በንብረቱ ላይ መኖር ስላለ ደህንነት ለማረጋገጥ በአስቸኳይ ጥገናዎች ማድረግ ማስፈለጉ አንደኛው ይሆናል። በዚህ ላይ የሚካተቱ ነገሮች እንደ የጋዝ ማንጠብጠብ፤ የውሃ ማሞቂያ አሰራር መበላሸት ወይም የገንዳ አጥር ጕዳት ብልሽት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በተከራየ ንብረት ላይ ጥገናዎች/Repairs in rental properties ላይ ማየት
በአስቸኳይ ጥገና እንዲደረግ ካስፈለግዎት
- ለርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ በጽሁድ አድርገው መንገርና ወዲያውኑ ማስተካከል አለባቸው። ጥያቄዎን በጽሁፍ አድርጎ ማቅረቡ ጥሩ ዘዴ ነው። ምንም እንኳን መጀመሪያ ለኪራይ አቅራቢ ወይም ለንበረት ተወካዩ በስልክ አድርገው ቢያነጋግሩም በጽሁፍ አድርጎ ማሳወቅ።
- በፍጥነት ጥገናውን ካላካሄዱ፤ ለጥገና የሚሆን ገንዘብ እስከ $2500 እራስዎ መክፈል ይችላሉ።
- በጽሁፍ ላቀረቡት ጥገና ሥራ የተካሄደበትን ክፍያ ደረሰኝ በሙሉ ስለማስቀመጥ ያረጋግጡ።
- ይህንን ቅጽ/this form በመጠቀም ለጥገና ሥራ ያወጡትን የክፍያ ገንዘብ እንዲመለስ ለኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ መጠየቅ። ለኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ ይህን ቅጽ በደረሳቸው በ 7 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መመለስ አለባቸው።
- አስቸኳይ ለሆነ ጥገና የመክፈል አቅም ከሌለዎት፤ የጥገና ክፍያው ከ $2500 ዶላር በላይ ከሆነ ወይም የኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ መክፈል ካለበት እርስዎ ላለመክፈል እምቢ ማለት ይችላሉ፤ ለምክር ለእኛ/us መደወል።
አስቸኳይ ጥገና ስለማስፈለጉ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ለአስቸኳይ ጥገና ሙሉ ዝርዝር/full list of urgent repairs የሚለውን ማንበብ።
በንብረቱ ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ መኖር ከቻሉ ጥገናው አስቸኳይ አይደለም። አስቸኳ ባልሆነ ጥገና ላይ የሚካተቱ ነገሮች እንደ የተሰበረ ቁም ሳጥን ወይም የእቃ ማጠቢያ መሳሪያን ይሆናል። የኪራይ አቅራቢ አሁንም አስቸኳይ ላልሆኑት ጥገናዎች በ 14 ቀናት ውስጥ ማስተካከል አለበት።
አስቸኳይ ላልሆነ ጥገና ከፈለጉ:
- ጥገናው እንዲካሄድ ለርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ በጽሁፍ አድርገው መጠየቅ። በኢሜል ወይም በደብዳቤ አድርገው መላክ ይችላሉ ወይም ይህን ቅጽ/ this form መጠቀም ይችላሉ
- የተላኩትን ደብዳቤዎች፤ ኢሜሎች፤ ጽሁፋዊ መልእክቶች/ተክስቶች፤ ቅጾች እና ሪፖርቶች ቅጂን በሙሉ ማስቀመጥ፤ ስለዚህ ችግር ከተፈጠረ ወይም ክርክር ከተፈጠረ ለጠየቋቸውና ለወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ የሚያሳይ ማስረጃ ይኖርዎታል።
- የኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካዩ ለቀረበለት የጥገና ጥያቄ በ 14 ቀናት ውስጥ ጥገናውን ካላካሄደ ለእኛ/us መደወል ወይም ለጥገና ጥያቄ ለ ቪክቶሪያ ሲቪል አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት/VCAT ማመልከት።
የስምምነት ውልን እንደገና ማደስ
የርስዎ ኪራይ ስምምነት ውል በሚያልቅበት ጊዜ፤ ሁልጊዜ ከንብረቱ አይወጡም። በንብረቱ ላይ መቆየት ከፈለጉ እና አዲስ የስምምነት ውል መፈረም ከቻሉ ወይም በየወሩ የሚታደስ አዲስ ስምምነት መፈረም ከቻሉ ለርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ ማነጋገር። ስለ የኪራይ ስምምነት (ኩንትራት) ስለማደስ/Renewing a rental agreement (lease) በበለጠ ማንበብ።
የስምምነት ውልን ስለመጨረስ
የኪራይ ስምምነት ውል በተለያዩ ምክንያቶች ማቆም ይችላል። አንዳንድ ከተለመዱ ምክንያቶች:
- ተከራዩ ለመልቀቅ ከወሰነ
- የስምምነቱ መጨረሻ ቀን ከደረሰ
- የኪራይ አቅራቢው በንብረቱ ለመግባት፤ ለመሸጥ ወይም ከፍተኛ የእድሳት ጥገና ማድረግ ከፈለገ
ተከራዩ የቤት ኪራይ ክፍያን ካቆመ፤ ሌሎችን በአደጋ ማጋለጥ፤ በንብረቱ ላይ ከፍተኛ ጕዳት ማድረስ ወይም በስምምነት ላይ ለተቀመጡት ደንቦች ከጣሰ ይሆናል።
ተገቢ በሆነ የኪራይ ስምምነት ውል ማቆም ስለመቻል የበለጠ መረጃ በተከራዮች ስለሚሰጡት ማስጠንቀቂያ/Renters giving notice ወይም ለሁከት፤ አደገኛ ባህሪ እና ከፍተኛ አደጋ/Immediate notice for violence, dangerous behaviour and serious damage ላይ ይታያል።
ያለዎትን ስምምነት ውል ማቆም ከፈለጉ
ከተከራዩት ቤት መውጣት ሲፈልጉ፤ ለርስዎ ኪራይ አቅራቢ ትክክለኛ መጠን ማስጠንቀቂያ/correct amount of notice መስጠት እና የንብረቱን ንጽህና በጥሩ ሄኔታ አድርጎ መልቀቅ እንዳለብዎት ነው።
- ምን ያህል ማስጠንቀቂያ ለእኛ መስጠት እንዳለብዎት ለማወቅ ከእኛ ጋር ማጣራት/Check with us። ይህ በርስዎ ላይ ባለው ሁኔታ ሊለያይ ይችላል።
- ከቤት ለመልቀቅ እቅድ ሲኖርዎት በጽሁፍ አድርገው በኢሜል ወይም በደብዳቤ ለኪራይ አቅራቢ ወይም ለተወካዩ መንገር።
- ለማንኛውም ያልተከፈለ ኪራይና የፍጆታ ክፍያዎች መክፈል።
- ስለ የማስያዣ ገንዘብዎ መመለስ/getting your bond back ለኪራይ አቅራቢ ወይም ለተወካዩ ማነጋገር።
- ንብረቱን ማጽዳትና የርስዎን እቃዎች በሙሉ ስለቁ መውሰድ።
- ምናልባት በማስያዣ ገንዘብ መመለስ ችግር ከተፈጠረ የንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርቱን ማስቀመጥ
- የሚገኙበትን አድራሻና የስልክ ቁጥር ከርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም ተወካይ ጋር ማስቀመጥ።
የማስያዣ ገንዘቡን ስለመመለስ
በኪራይ አቅራቢው የመጨረሻ ፍተሻ ያደርግና የንብረት ይዘት ሁኔታ ሪፖርቱን/ condition report በመጠቀም በንብረቱ ላይ የሆኑ ለውጦች ካሉ ያመዛዝናል። የተወሰነ ማስያዣ ገንዘብ ጥያቄ/claim some of the bond ላቀረቡበት ጥሩ ምክንያት ነው ብለው ያሰቡትን ይነግርዎታል።
በኪራይ አቅራቢው የተጠየቀውን ከማስያዣ ገንዘብ ምን ያህል መጠን ስለመሆኑ ካልተስማሙበት በማስያዣ ገንዘብ መጠየቂያ ቅጽ ላይ አይፈርሙ። ያለ ክፍያ በነጻ ምክር ለማግኘት እኛን ማነጋገር/Contact us።
በምንም ዓይነት ባልተሞላ ማስያዣ ገንዘብ መጠየቂያ ቅጽ ላይ አለመፈረም።
ቀደም ብሎ ስምምነት ውልን ስለማቆም (የውል ኩንትራት ስለማፍረስ)
ከተከራዩበት ንብረት ከኩንትራት ቀን በፊት መልቀቅ ከፈለጉ ወጪውን መክፈል ሊኖርብዎት ይችላል ታዲያ ኪራይ አቅራቢው የሚከፈለውን ገንዘብ አያጣም።
እንዲሁም ቤቱን ከለቀቁ በኋላ የኪራይ አቅራቢው በቀጥታ ሌላ ተከራይ ማግኘት ካልቻለ የቤት ኪራዩን በቀጣይነት መክፈል ይኖርብዎት ይሆናል።
ይሁን እንጂ የሚከፍሉት ወጪዎች ምክንያታዊ መሆን እንዳለበት እና የኪራይ አቅራቢው አዲስ ተከራዮች ለማግኘት ማንኛውንም ጥረት ማድረግ አለበት። ምክንያታዊ ያለው ወጪዎች ማለት አብዛኞች ሰዎች አግባብ ያለው ወጪ ነው ብለው ላመኑበት ነው። ምክንያታዊ ላለው ወጪዎች ምን እንደሆነ ህጉ በቀጥታ መግለጫ ስለማይሰጥ፤ ስለዚህ ሰዎች በምክንያታዊ ወጪዎች ላይ ካልተስማሙ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ለማመልከት VCAT/ apply to VCAT ናቅረብ ይችላሉ።
ሰለ ቀደም ብሎ ስምምነቱን ማቆም/ending an agreement early በበለጠ ማንበብ።
የኪራይ ስምምነት ውልን ለሌላ ስለማስተላለፍ
ቀደም ብሎ የስምምነት ውሉን ከማቆም እና ወጪዎችን ከመክፈል ባሻገር የስምምነት ኩንትራት ውሉን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችሉ ይሆናል።
ይህንን ካደረጉ የማስተላለፊያ ክፍያዎችን ማካሄድ እንደሚችሉ፤ ይሁን እንጂ እንደ ሥራው መጠን እነዚህ ክፍያዎች ምክንያታዊ መሆን አለባቸው። ሰለ ኪራይ ስምምነት ውል ለሌላ ስለማስተላለፍ/Transferring a rental agreement በበለጠ ማንበብ።
ከቤቱ እንዲወጡ ስለመጠየቅ (የማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ ስለማግኘት)
የኪራይ አቅራቢ ንብረቱን ለቀው እንዲወጡ ሊጠይቅ ይችላል፤ ነገር ግን ለበቂ ጥሩ ምክንያት ብቻ ይሆናል። ለምሳሌ:
- የኪራይ ስምምነቱ ውል ካለቀ
- ሰዎች በንብረቱ ውስጥ ለመኖር ብቃት ከሌላቸው
- ቢያንስ የ 14 ቀናት ያልተከፈለ የቤት ኪራይ እዳ ካለብዎት ነው።
ተከራዩ የሆነ ነገር ስላደረገ፤ የሆነ ነገር እንዲያደርግ ስለተናገረ ለማስወጣት የኪራይ አቅራቢ ማስጠንቀቂያ መስጠት እንደማይችል እና እንደ ተከራይ መጠን ለማድረግ ህጋዊ የሆነ መብት አላቸው።
ለምሳሌ፡ የኪራይ አቅራቢው ለተከራዩ እንዲለቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት የማይችለው:
- ለጥገና ሥራ ስለተጠየቀ
- የቤት እንስሳት እንዲኖረው ስለጠየቀ
- የቤት ኪራይ በመጨመር ስለመቸገር ይሆናል።
ይሁን እንጂ፤ የኪራይ አቅራቢው ለኪራይ ስምምነት ውል ማቆም የፈለገበት ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። የኪራይ አቅራቢው በሚያቀርባቸው ምክንያቶች ሁሉ እንዲለቁ መጠየቅ እንደሚችል እና ለርስዎ ምን ያህል ማስጠንቀቂያ መስጠት እንዳለበት ለማየት ከኪራይ ቤቶች ለመውጣት ማስጠንቀቂያ/Notice to vacate in rental properties ይቀርባል።
በማስወጣት ማስጠንቀቂያ ላይ ስለመቸገር
ከቤት ለማስወጣት ማስጠንቀቂያ ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ተሰጥትዎት ከነበረ፤ ወይም የርስዎ ኪራይ አቅራቢ የውሸት ወይም አግባብ የሌለው ምክንያት ሰጥቷል ብለው ካሰቡ ማስጠንቀቂያውን መቃወም ይችላሉ፤ ለበለጠ መረጃ እኛን ማነጋገር/Contact us።
ማስወጣት (የማስለቀቂያ ትእዛዝ ስለማግኘት)
ከቤት እንዲወጡ ተደርጎ እንደሆነ እና ያለ ክፍያ በነጻ ምክር ከፈለጉ እኛን ማነጋገር/Contact us።
ጠቃሚ ነገሮችን ማስታወስ
- በማንኛውም ነገር ላይ ምን እንደሆነ ሳይረዳዎት አለመፈረም።
- ምንም እንኳን ህጋዊ ቢመስልም ባልተሞላ ባዶ ቅጽ ላይ አለመፈረም።
- ለፈረሙበት ማንኛውንም ነገር ቅጂውን ማስቀመጥ።
- ከርስዎ ኪራይ አቅራቢ ወይም የንብረት ተወካይ ጋር ያካሄዱትን ግንኙነት ቅጂዎችን ማስቀመጥ።
- ለሆነ ነገር በሚከፍሉበት ጊዜ ደረሰኝ መጠየቅ።
- የርስዎን ማስያዣ ገንዘብ ደረሰኝ እና ለቤት ኪራይ ወይም ጥገና ለተከፈለ ማንኛውንም ሌላ ደረሰኝ ደህንነት ባለው ቦታ ላይ ማስቀመጥ።
ስለ የቤት ኪራይ ችግር ወይም ጥያቄ ካለዎት በነጻ ምክር ለማግኘት እኛን ማነጋገር።
ከአስተርጓሚ ጋር ለቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ለማነጋገር በስልክ 13 14 50 መደወል