የመንገድ አታላይ ሰራተኞች

Skip listen and sharing tools

Note: If this page does not display correctly, download a copy instead: Travelling con men - Amharic (PDF, 85KB).

የመንገድ አታላይ ሰራተኞች አድበስብሰው የሚያመልጡ ነጋዴዎች ሲሆኑ የቤት በሮችን በማንኳኳት እና በትናንሽ ንግድ ቦታዎች በመሄድ የጥገና ሥራ እናካሂድ የሚሉ ናቸው።

ብዙጊዜ የሚታዩት በሞቃት አየር ወቅት ላይ እና ከተፈጥሮ መአት አደጋ ማለት እንደ ጐርፍ፣ እሳትና ማእበል በኋላ ሲሆን ይህም በአደጋው የተጋለጡት ሰዎች ጽዳት ሲያካሂዱ ወይም ንብረታቸውን በሚጠግኑበት ጊዜ ይሆናል።

የመንገድ አታላይ ሰራተኞች ሥራዎችን እናቀርባለን ማለት እንደ በርካሽ ዋጋ የመተላለፊያ ወለል ማስተካከል፣ ቀለም መቅባት፣ የጣራ ጥገና እና ስጋጃ ምንጣፍ ማጽዳት ያሉ ሥራዎችን ለማካሄድ። ይህ 'ለዛሬ ብቻ' የሚሰጥ ልዩ ዋጋ በማለት ብዙ ጊዜ ሰዎችን ይገፋፋሉ።

ለምን አያስወግዷቸውም?

የመንገድ አታላይ ሰራተኞች ሥራውን ከመጀመራቸው በፊት በቅድሚያ ክፍያው በጥሬ ገንዘብ እንዲሰጣቸው ይጠይቁና ሲከፍሏቸው ወዲያውኑ ከአካባቢ መሰወሩ የተለመደ ነው።

የሆነ ሥራም ካካሄዱ ብዙጊዜ ያላለቀ ወይም ጥራት የሌለው ነው።

በፍጥነት ይቀርቡና ብዙጊዜ የመጀመሪያ ስማቸውንና የሞባይል ቁጥር ይሰጣሉ - ታዲያ ከዚያ በኋላ እነሱን ማግኘቱ ከባድ ይሆናል።

ምን ማየት እንዳለብዎት?

ከዚህ በታች ስላሉት ሰዎች መጠራጠር:

  • በድንገት የርስዎን በር በማንኳኳት ስለሚከተሉት እናደርጋለን ለሚሉት:
    • የቤት ቀለም መቅባት
    • አትክልት ቦታ ሥራ ወይም ዛፎችን መቁረጥ
    • የመተላለፊያ መንገድ ወለል ማስተካከል
    • ለርስዎ ጣራ ጥገና ሥራ
  • 'ለዛሬ ብቻ' የሚል ቃል በመጠቀም በርካሽ ዋጋ ድርድር ማቅረብ
  • በቅድሚያ በጥሬ ገንዘብ መጠየቅ
  • ለሥራው የሚሆን ገንዘብ ከባንክ ለማውጣት በመኪና እወስድዎታለሁ በማለት
  • እነሱ ያቀረቡትን እንዲቀበሉ ጫና ይፈጥራሉ
  • አሁኑኑ ሥራውን ማካሄድ እንችላለን ምክንያቱም በአቅራቢያ የነበረ ሌላ ሥራ ስለተሰረዘ በማለት።

እርስዎን ስለመከላከል - ከመንገደኛ አታላይ ሰራተኞች ጋር ስለመደራደር ምክሮች

በሩን የሚያንኳኳ የመንገድ አታላይ ሰራተኛ ነው ብለው ከተጠራጠሩ መልስ አይስጡ።

ካነጋገሯቸው፤ ህጉን እየጣሱ ስለሆነ እንዲሄዱ ይጠይቋቸው።

የሚቀረበን ርካሽ ዋጋን ድርድር አለመቀበል። ከጊዜ በኋላ ብዙ ወጪ ሊያስከፍል ይችላል።

በቤትዎ ሥራው እንዲካሄድ ከፈለጉ:

  • ለርስዎ ተስማሚ የሆነ የዋጋ ተመን በአካባቢው ማፈላለግ
  • በጽሁፍ አድርጎ የዋጋ ተመን ለሚያቀርቡ ነጋዴዎች መጠቀም
  • ቀደም ሲሉ ለነበሩ የደንበኞች አድራሻ በመጠየቅ የሰጡትን ምስክርነት ማረጋገጥ ይችላሉ
  • እስከሚዘጋጁ ድረስ በምንም ስምምነት ወረቅት ላይ አለመፈረም
  • የነጋዴውን ሙሉ ስምና ምዝገባ ወይም የፈቃድ ዝርዝር መግለጫን (ካለ) መጠየቅ ስለዚህ በነሱ የኢንዱስትሪ ባለሥልጣ ላይ ማጣራይ ይችላሉ።
  • የንግድ ቁጥሩን መጠየቅ ስለዚህ ነጋዴው ከነሱ ስለመሥራቱ ማጣራት ይቻላል።

በተለይ መአት አደጋ ከተፈጠረ በኋላ ጥገናውን በጥሬ ገንዘብ ለማስጠገን 'ለዛሬ ብቻ' በሚል የዋጋ አቅርቦት በሚሰጥ ማንኛውም ሰው ላይ ይጠንቀቁ። በመአት አደጋ ጊዜ ምክር ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የእኛ Advice in a disaster የሚለውን ገጽ ማየት።

በመንገድ አታላይ ሰራጠኞች እርምጃ ስለመውሰድ

አድበስብሰው ስለሚያመልጡ ነጋዴዎች ማህበረሰብዎ እዲጠነቀቅ እንዲረዳን፤ እባክዎ ይህንን ገጽ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ እና በአማርኛ ቋንቋ ስብሰባዎች በኩል ማሳወቅ ነው። በአካባቢዎ የመንገድ አታላይ ሰራተኞች ስለመኖራቸው የሚያውቁ ከሆነ:

  • በተቻለዎ መጠን መረጃ መመዝገብ፤ እንደ ስማቸውና የተሽከርካሪ ታርጋ ቁጥር
  • ለአካባቢዎ ፖሊስ ስለነሱ ሪፖርት ማድረግ