If this page does not display correctly, download a copy instead: Buying a car - Amharic (PDF, 215KB).
መኪና በሚገዙበት ጊዜ ትክክለኛ የሆነ ውሳኔ ለማካሄድ የሚከተለው መረጃ ይረዳዎታል።
መኪና ከመግዛትዎ በፊት
1. ያፈላልጉ
- በጋዜጣ ላይ የወጣን ዋጋ እና በኢንተርኔት ያለን ዋጋ ማነጻጸር. ወደ ተለያየ የመኪና መሸጫ ቦታዎች መሄድ።
- ስለዋጋ መደራደር ይችላሉ፤ በተለይ ጥቅም ላይ የዋለ መኪና የሚገዙ ከሆነ።
- ስለ መኪና ይዘት፣ ነዳጅ ወጪ፣ ክፍሎች ደህንነት እና ሌላ ዝርዝር መግለጫ በተመለከተ መረጃ በመኪና መፅሄት እና በድረገፅ ላይ ሊቀርብ ይችላል።
- ስለተለያዩ መኪናዎች የወደፊት ጥገና ወጪዎች በተመለከተ መረጃ ማግኘት። ለምሳሌ፡ ከውጭ አገር የመጡ መኪናዎችን አገልግሎት ወይም ጥገና ለመስጠት የበለጠ ሊወደድ ይችላል።
- የሚከተሉት ምንጮች ጥሩ መረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ:
2. ለፋይናንስና ዋስትና ኢንሹራንስ ማፈላለግ
- አብዛኛው የሞተር መኪና ነጋዴዎች የገንዘብ ፋይናንስ ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ለርስዎ ጥሩ አማራጭ ወይም ርካሽ ላይሆን ይችላል።
- እንዲሁም ብድር የሚያቀርቡ ባንኮች፣ ክረዲት ዩኒየን እና ሌላ የገንዘብ ፋይናሻል ተቋሞችን የሚያስከፍሉትን መጠንና ዋጋ ማጣራት።
- የብድር ማመልከቻው እስኪጸድቅ ድረስ መኪና ለመግዛት የኮንትራት ውል አይፈርሙ።
- ምንም እንኳን ግዴታ ባይሆንም መኪና ከገዙ ኢንሹራንስ ዋስትና ማስገባቱ ጥሩ ሀሳብ ነው። አደጋ ከደረሰብዎ ወይም መኪናዎ ከተሰረቀ፣ ከተበላሸ ወይም ያለምክንያት ከተሰባበረ ለሚከሰተው ወጪ በዋስትና ኢንሽራንስ ሊሸፈን ይችላል።
- ዋስትና ኢንሹራንስ ከማንኛውም አቅራቢ ድርጅት ማግኘት ይችላሉ። የገንዘብ ባጀት ሲያወጡ የዋስትና ኢንሹራንስ ወጪንም ስለመጨመርዎ ማረጋገጥ።
- የዋስትና ኢንሹራንስ ክፍያ እንደ መኪናዎቹ ዓይነትና የርስዎ አነዳድ ደረጃ ምጣኔ ይለያያል። እንዲሁም መኪናውን የሚነዳ ሰው ወይም የእርስዎ እድሜ ከ25 ዓመት በታች ከሆነ የበለጠ ሊያስከፍልዎ ይችላል።
3. መኪና ለመግዛት ጥሩ መንገድ መምረጥ
- በአጠቃላይ አዲስ መኪናዎች የሚገዙት በሞተር መኪና ፈቃድ ባለው ነጋዴ በኩል ይሆናል።
- ይሁን እንጂ፤ ያገለገለ መኪና መግዛት የሚችሉት በግል ሽያጭ ወይም በጨረታ ማካሄጃ መጠለያ በኩል ይሆናል። ለርስዎ የሚስማማዎትን ስለመምረጥዎ ያረጋግጡ።
- አንዳንዴ መኪና ለመግዛት በግል ሽያጭ በኩል ወይም ከጨረታ ማካሄጃ መጠለያ መግዛቱ ረከስ ያለ ሲሆን ነገር ግን በሚገዙበት ጊዜ ከፈቃድ ካለው የሞተር መኪና ነጋዴ ላይ ብዙ ህጋዊ መብቶችን ስለማይገኝ አደገኛ ይሆናል። እንዲሁም መኪናውን ከመግዛትዎ በፊት ፍተሻ ማድረግ አይችሉ ይሆናል።
- ፈቃድ ካለው የሞተር መኪና ነጋዴ ላይ ከገዙ ብዙ ህጋዊ መብቶችን ያገኛሉ። ለምሳሌ፡ መኪና ለመግዛት ኮንትራት ውል ከፈረሙ በኋላ የሶስት ቀን ሀሳብ መቀየሪያ ጊዜ ያገኛሉ።
- እንዲሁም ፈቃድ ካለው የሞተር መኪና ነጋዴ ላይ ከገዙ ዋስትና ማረጋገጫ ያገኛሉ። የዋስትና ማረጋገጫ ማለት መኪናውን ከገዙ በኋላ አንዳንድ ብልሽት ከፈጠረ መኪናውን መግዛት አይኖርብዎም።
- ፈቃድ ያለው ነጋዴ እና የግል ሽያጮች ሁለቱም በመስመር ላይ መኪና ይሸጣሉ። በአካል ያላዩትን መኪና ስለመግዛት በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎ።
- መኪናውን ከመግዛትዎ በፊት እርስዎ በሚያምኑት ገለልተኛ የሆነ መካኒክ መኪናውን ማስፈተሽ።
- በመስመር ማስታወቂያ ላይ ከተገመተው የመኪና ዋጋ ረከስ ያለ የሽያጭ መኪና ካዩ ጥንቃቄ ማድረግ። ይህ ለመኪናው ማቆያ ማስያዣ ገንዘብ በቅድሚያ እንዲከፍሉ ተብሎ መኪና በሌለበት ለተንኰል የወጣ ዘዴ ሊሆን ይችላል።
መኪና በሚገዛበት ጊዜ
1. የኮንትራት ውል ስለመፈረም
- የኮንትራት ውሉን ለመፈረም የግዴታ ስሜት አለማሳደር። ለኮንትራት ውሉ እስኪረዳዎ ጊዜ መውሰድ። ኮንትራቱ ካልተረዳዎት ለሚረዳ ሰው ማሳየት።
- መኪናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዩ ኮንትራቱን ላለመፈረም መሞከር። ይህን መኪና ከመሸጪያ ቦታ ከመውሰድዎ በፊት ለርስዎ ትክክለኛ ስለመሆኑ ጊዜ ወስዶ ማጣራት።
- በኮንትራቱ ውስጥ የማይስማሙበት ነገር ካለ፤ ከሽያጩ ጋር መነጋገር። የኮንትራቱን ጊዜ ገደቡን መቀየር ይቻላል።
2. ሀሳብዎን ስለመቀየር
- ያስተውሉ፤ መኪና ለመግዛት ከፈቃድ ካለው የሞተር መኪና ነጋዴ ጋር ከፈረሙ፤ መኪና ስለመግዛት ‘የሀሳብ መቀየሪያ’ ጊዜ ሶስት የሥራ ቀናት ይሰጥዎታል። ይህ ማለት መኪና ስለመግዛት ያለዎትን ሀሳብ ለመቀየር ሶስት የሥራ ቀናት ይኖርዎታል።
- በሶስት ቀናት ውስጥ ሀሳብዎን ለመቀየር ከወሰኑ ታዲያ ነጋዴው ገንዘብ ሊያስቀር ይችላል:
- $400 ዶላር ወይም ከሽያጭ ዋጋ ከመቶ ሁለት እጅ፤ ከፍተኛ የሆነን (ለአዲስ መኪናዎች), ወይም
- o $100 ዶላር ወይም ከሽያጭ ዋጋ ከመቶ አንድ እጅ፤ ከፍተኛ የሆነን (ለአገለገሉ መኪናዎች)።
3. የዋስትና ማረጋገጫ
- ያስተውሉ፤ ፈቃድ ካለው ነጋዴ መኪና ከገዙ፤ የዋስትና ማረጋገጫ ያገኛሉ። ለወደፊት በመኪናው ላይ ለሚፈጠር ብልሽት ማስጠገኛ ክፍያ እንዳያካሂዱ በዋስትና ማረጋገጫ በኩል ይሸፈናል። ለአዲስ መኪናዎች የዋስትና ማረጋገጫ ጊዜ ለየት ያለ ሊሆን ይችላል። በግል ወይም በጨረታ መሸጫዎች ላይ የዋስትና ማረጋገጫ አይኖርም።
- ፈቃድ ካለው ነጋዴ ያገለገለ መኪና ሲገዙ የዋስትና ማረጋገጫ መስጠት ያለበት ምናልባት:
- o የመኪናው እድሜ ከ10 ዓመት በታች ከሆነ፤ እና
- o የመኪናው 160,000 ኪሎ ሜትር በታች ከተጓዘ ይሆናል።
- ላገለገለ የመኪና ህጋዊ የዋስትና ሁኔታ የሚያልቀው ለሶስት ወራት ወይም 5000 ኪሎ ሜትር፣ ቀድሞ በደረሰው ይሆናል። መኪናው ባለው እድሜ መሰረት በጥሩ ሁኔታ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ሲባል በዋስትና ማረጋገጫ ጊዜ ለሚከሰት ማንኛውም ብልሽት ማስጠገኛ በነጋዴው በኩል መሸፈን አለበት።
- ህጋዊ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ ጊዜ ካለቀ በኋላም ቢሆን በመኪናዎ ላይ ችግር ካለበት በአውስትራሊያ ተጠቃሚ ህግ መሰረት መብትዎ የተጠበቀ ነው። ይሁን እንጂ የመከላከያ ደረጃ እንደ መኪናው እድሜና ሁኔታ ይወሰናል።
- የመኪና ደላላዎች የዋስትና ማረጋገጫ ጊዜን ሊያራዝሙት ይችሉ ይሆናል። በነዚህ የዋስትና ማረጋገጫ ጊዜ ማራዘሚያ የሚካተተው በመጀመሪያ የሰራው ፋክተሪ የነበረን ዋስትና ማረጋገጫ ሲሆን፤ ይህም በአብዛኛው ተጨማሪ ክፍያ አለው። የዋስትና ማረጋገጫ ጊዜ ማራዘሚያ ላለመውሰድ ይችላሉ።
4. በርግጠኛ ምን ያህል እንደሚከፍሉ ማወቅ
- ፈቃድ ካለው የመኪና መሸጪያ ቦታ መኪና ሲገዙ ታዲያ ‘ጠቅላላ’ ዋጋው ስለማወቅዎ ማረጋገጥ። በጠቅላላ ዋጋ ውስጥ የሚካተት ተጨማሪ ክፍያ እንደ የቀረጥ ማሳተሚያ እና መመዝገቢያ ይሆናል።
መኪና ከገዙ በኋላ
1. መኪናዎን ሰርቪስ ስለማስደረግ
- መኪናዎን ሁልጊዜ ሰርቪስ ስለማስደረግዎ ማረጋገጥ። ይህ የመኪናውን ሁኔታና ዋጋ እንዲጠበቅ ይረዳል።
2. የመኪና ጥገና
- መካኒክ በሚመርጡበት ጊዜ በማሕበር ውስጥ ማለት እንደ RACV እና በቪክቶሪያ አውቶሞቢል ይንግድ ምክር ቤት (VACC) የታቀፉ ስለመሆናቸው ማጣራትና አባላቱ የስነ ምግባር ደንብ መከተል አለባቸው።
- መኪናዎን ለሰርቪስ በሚወስዱበት ጊዜ፤ ሊደረግ የፈለጉትን ሥራ በግልጽ ለመካኒኩ ማስረዳት ነው።
- በቅድሚያ በጽሁፍ ተደርጎ የዋጋ ተመን ማግኘት።
- አንዳንድ ጊዜ መካኒኩ በመኪናው ላይ ሌላ ብልሽት ሊያገኝ ይችላል። ታዲያ እርስዎ ያልፈቀዱትን ተጨማሪ ሥራ ከመጀመሩ በፊት መካኒኩ ስለመደወሉ ማረጋገጥ ነው። ጥገና እንዲካሄድ ከመስማማትዎ በፊት ማንኛውም የዋጋ ተመን በጽሁፍ ስለመሆኑ ማረጋገጥ።
- እርስዎና መካኒኩ ስለ መኪናዎ ጥገና ዋጋ መስማማት ካልቻላችሁ፤ ችግሩን ለመፍታት የቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ሊረዳዎ ይችላል። ለዝርዝር መርጃ የእኛን ለክርክር መፍትሄ ማስገኛ ገጽ/ ማየት ነው።
መኪናዎች መከራየት
- መኪና ከተከራዩ፤ ታዲያ ተስማሚ ጥራት ያለው መኪና ስለመሆኑ አከራይ ኩባንያው ማረጋገጥ አለበት።
- በመኪና ኪራይ ስምምነት ላይ ከመፈረምዎ በፊት አንብበው ስለመረዳትዎ ማረጋገጥ። ካልተረዳዎ መርዳት ለሚችል የሆነ ሰው ማሳየት።
- Mበመኪናው ላይ የሆነ ጉዳት ካለበት ማን ሃላፊነት እንደሚወስድ ስለማወቅዎ ማረጋገጥ። ለምሳሌ፡ ምን ያህል ነው ወጪ ነው በዋስትና ኢንሹራንስ የሚካተት?