ማጭበርበር ማለት ከሌሎች ሰዎች ገንዘብ ለመስረቅ ወይም ግላዊ የሆነን መረጃ ለመውሰድ በጨካኝ አጭበርባሪዎች የሚፈጠር የማታለያ ዘዴ ነው።
በተንኮል ማጭበርበሩ ከሎተሪዎች፣ ከመስመር ላይ ሽያጭ፣ ዘላቂነት ከሌለው ፍቅር፣ ከገንዘብ ኢንቨስትመንት፣ ከዋጋ ተመላሽ እና ከቤት ኪራይ ንብረቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ሰዎችን ለማነጋገር አጭበርባሪዎቹ ስልክ፣ ኢሜል፣ የጽሁፍ መልእክትና በፖስታ መልእክት ይጠቀማሉ። ሶስት ዋና የተለመዱ ተንኮሎችን ለይተው በማወቅ እራስዎን ለመከላከል የሚረዳ አንዳንድ መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል።
በሎተሪ ስም ማጭበርበር
አጭበርባሪዎቹ ትክክለኛ በሚመስል ደብዳቤ፣ ኢሜል፣ የጽሁፍ መልእክት ወይም በማሕበራዊ ብዙሀን መገናኛ አድርገው የሎተሪ እጣ እንደደረስዎ ዜና ይልካሉ። የተገኘው ሽልማት ለእረፍት፣ ለስማርትፎን/ smartphone ወይም ለእቃ መግዣ ደረሰኝ/ቮቸር ሊሆን ይችላል። የተባለውን ሽልማት ለመጠየቅ ታክስ/ግብር ወይም ክፍያ ማካሄድ ወይም የባንክ አካውንት ዝርዝር መረጃ መላክ እንዳለባቸው ይነግሯቸዋል።
በዚህ ማጭበርበር ላይ መካተት ከሚችሉት አንዳንድ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች:
- ባልገቡበት ሎተሪ ወይም ውድድል ላይ ሽልማት ስለማግኘት
- ስለርስዎ ግላዊ መረጃ በስልክ ቁጥር ለመናገር ወይም በኢሜል አድርገው እንዲልኩት ይጠየቃሉ
- ላገኙት ሽልማት ጥያቄ ለማካሄድ ክፍያ ወይም የባንክ ዝርዝር መረጃዎን መላክ አለብዎ
- የፖስታ ቤት(PO) ሳጥን ቁጥር፣ የኢሜል አድራሻ ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥር እንደ መገናኛ አድራሻ ተደርጎ ይሰጣል (የመንገድ አድራሻ አይቀርብም)።
በተመላሽ ዋጋ ስም ማጭበርበር
አጭበርባሪዎች ከመንግሥት አካል፣ ከባንክ ወይም ከሌላ የታወቀ ድርጅት እንደሆኑ ያስመስሉና ከዚያም የሚከፈል ገንዘብ አለህ በማለት፤ ነገር ግን ገንዘቡን ‘ከመጠየቅህ' በፊት መጀመሪያ ለአስተዳደር ወይም ለተመሳሳይ የወጣ ክፍያን ማጠናቀቅ አለብህ። እንዲሁም አንዳንድ አጭበርባሪዎች የጡረታ ሙሉ ክፍያችሁ አልተሰጠም ወይም በፍጆታ ክፍያ መጠየቂያ ላይ እላፊ ስለከፈላችሁ ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ ማግኘት ትችላላችሁ በማለት ይናገራሉ።
ትክክለኛ ባንክ፣ የንግድ ድርጅት ወይም መንግሥታዊ ድርጅት በምንም ተአምር ደውለው የሚከፈልዎ ገንዘብ አለዎት ነገር ግን ይህን ለማግኘት መክፈል አለብዎት አይሉም።
ዘላቂነት በሌለው ፍቅር ማታለል
አጭበርባሪዎች ህጋዊ በሆነ ድረገጽ ላይ ተበዳዮችን ይቀጥራሉ። አንዴ ፍላጎቱ ከተመሰረተ በኋላ ወደ ግላዊ ኢሜል፣ ስልክ መደወል ወይም ወደ ፈጣን መልእክት ግንኙነት ይሻገራሉ። አጭበርባሪው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በመስመር ላይ ከተበዳዩ ጋር ግንኙነት በማዳበር ወደ እምነትና በፍቅር ስሜት እስከመዛመት ደረጃ ድረስ ይሄዳል።
አጭበርባሪው ቀስ በቀስ ስለ ገንዘብ መፈለጉ ታሪክ ሲፈጥር፤ ይህም ብዙጊዜ ከመታመም ወይም ከቤተሰብ ጉዳት ወይም ለአንድ ነገር ገንዘብ ከማውጣት ጋር በተዛመደ ይሆናል። ምንም እንኳን ቤተሰብ ወይም ጓደኞች ይህ ሰው አታላይ ነው ቢሉም በዚህ ደረጃ ላይ ተበዳዩ በፍቅር ስሜት ላይ ስለወደቀ ገንዘቡን ለመላክ ዝግጁ ነው። ገንዘቡን አንዴ በተለግራም ወይም በገንዘብ ማስተላለፍ በኩል ከተላከ ገንዘቡን እንደገና ለመመለስ አይቻልም።
በራስዎ ለመከላከል - ማስታወስ ስለሚገባ ጠቃሚ ነጥቦች
- እውነተኛ ስለመሆኑ በጥሩ ሁኔታ ከታየ፤ ምናልባት ሊሆን ይችላል
- ባልታወቁ ኢሜሎች፣ ስልክ ጥሪዎች ወይም ደብዳቤዎች በኩል ጥያቄ ያልተደረገበት የገንዘብ እርዳታ አለዎ ወይም የርስዎ ገንዘብ አለ በሚልበት ጊዜ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎ
- ስለተባለው ሽልማት ወይም ተመላሽ ገንዘብ ብለው ገንዘብ ወይም የባንክ ዝርዝር መረጃዎን በምንም አለመላክ
- ሎተርይ ከገዙ ወይም ለማሸነፍ እጣ ውስጥ ከብተው ከሆነ ማጣራት፤ ታዲያ ህጋዊ የሆኑ ሎተሪዎች ያሸነፉትን ሽልማት እንዲወስዱ ሌላ ክፍያ አይጠይቁም
- በገንዘብ መክፈያ ትእዛዝ እና በቴሌግራም አድርጎ ለምንም ነገር አለመክፈል - ሁልጊዜ ደህንነቱ በተረጋገጠ ዘዴ መጠቀም ማለት እንደ ክረዲት ካርድ/credit card ወይም PayPal አድርጎ መክፈል
- በታወቁ የባንኮች ወይም ሌላ ድርጅቶች ህጋዊ አርማ አስመስሎ በሚጠቀሙ የውሸት ድረገጾች አውቆ መጠንቀቅ - የሚቀርብልዎ ትክክለኛ ስለመሆኑ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ሁልጊዜ ለባንኩ ወይም ለድርጅቱ በቀጥታ ደውሎ ማጣራት ነው።
- የንግድ ድርጅቱን ለማግኘት በቀረበው ኢሜል መርበብ ላይ አለመጠቀም። ለማነጋገር የአድራሻ መረጃ ለመፈለግ ሁልጊዜ በመፈለጊያ መሳሪያ፤ በተለፎን ማውጫ ወይም በሌላ ተጽእኖ በሌለበት ምንጭ ላይ መጠቀም
- ቀደም ሲል በአካል ላልተገናኙት ሰው፣ ምንም እንኳን ቢያነጋግሩትም ወይም ስጦታ ቢያገኙም በምንም መልኩ ገንዘብ አለመላክ
- በመስመር ላይ ስለተገናኙት ሰው አሳሳቢ ጉዳይ ካላቸው፤ ስለዚህ የርስዎ ቤተሰብ ወይም ጓደኞች የሚሉትን መስማት
- በመስመር ላይ በቀረበው የቀጠሮ ስእል ከቀረበው ዝርዝር መግለጫ ጋር ካልተመሳሰለ ወይም ከመጋዘን ላይ የተወሰደ መስሎ ከታየ ጥንቃቄ ማድረግ ነው።/li>
በማጭበርበር ላይ እርምጃ ስለመውሰድ
የተጭበረበሩ መስሎ ከታየዎት ስለ አደጋው ሪፖርት ለማድረግ ወዲያውኑ ያነጋግሩን። በሁኔታዎ ላይ ተመርኩዞ ገንዘብዎ በክሬዲት ካርድ ሰጭው ወይም በባንኩ በኩል ሊመለስልዎት ይችል ይሆናል።
ገንዘብዎ ሊመለስልዎት ካልተቻለም ስለ ሁኔታው በቪክቶሪያ ለደንበኛ ጉዳይ/ Consumer Affairs Victoria ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ታዲያ በሌሎች ላይ መታለል እንዲቆም እንደ መረጃ ይረዳናል።
ማጭበርበር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል በበለጠ ለማወቅ በስተቪስ ስካም ትምህርት ቤት/ Stevie's Scam School ቪዲዮ ለደንበኞች እና ለአነስተኛ ንግድ ሥራዎች የሚለውን በ Consumer Affairs Victoria /ቪክቶሪያ ደንበኛ ጉዳይ ድረገጽ ላይ ማየት።